አለቃ ገብረሃና እና አህያ ነጂው
በያለምጌታ ማሞ የተተረከ
አንድ አለቃ ገብረሃና የተባሉ ብልህና አዋቂ ሰው ነበሩ፡፡ እኝህ ሰው በብልህ መልሶቻቸውና ሰውን በመሳደብ ይታወቁ ነበር፡፡
ታዲያ አንድ ቀን አንድ አህያ ይነዳ የነበረ ሰው በአለቃ ገብረሃና ደጅ ሲያልፍ ያያቸውና በጭንቅላቱ ብቻ ሠላምታ ሰጥቷቸው ያልፋል፡፡
አለቃም “እንደምንድናችሁ?”በተለምዶ ይህ አባባል አንድን ሰው በማክበር የሚባል ነው፡፡) ብለው ይመልሳሉ፡፡
የአህያውም ነጂ በአንድ ሥፍራ ሲደርስ አለቃ ገብረሃናን አይቶ እንደነበር ሲጠየቅ “አዎ፤ አይቻቸዋለሁ፡፡” አለ፡፡
“ታዲያ ሠላምታ እንዴት ሰጡህ? አልሰደቡህም?” ብለው ቢጠይቁት
እሱም “እረ አልሰደቡኝም! ሠላምታም ሰጥተውኛል፡፡” አለ፡፡
“ምን ብለው?” ሲሉትም “’እንደምንድናችሁ?’ ብለው፡፡” ብሎ ይመልሳል፡፡
“ታዲያማ ሰድበውህ የለ እንዴ!? አንተንም እንደኩራተኛ አህያ ቆጥረውሃል እኮ!” አሉት፡፡
እሱም በዚህ ተበሳጭቶ ወደ አለቃ ገብረሃና በመሄድ ደብድቦ በመንገድ ዳር ጥሏቸው ይሄዳል፡፡
በዚያ ያልፍ የነበረ አንድ ሰው “ምን ሆኑ?” ብሎ ቢጠይቃቸው አለቃም “አንድ አህያ እግሬን ሰብሮኝ ሄደ፡፡” ብለው መለሱ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|