የአባትየው አስተምሮት
በኦባንግ ኦቦቲ የተተረከ
በአንድ ወቅት በኦቦቦ ቀበሌ ፖኬዲ መንደር የሚኖር አንድ ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው ታዲያ በልጁ ስንፍና ያዝን ነበር፡፡
ታዲያ አንድ ቀን ለጓደኛው እንዲህ ብሎ ኑዛዜውን ነገረው፡፡
ጓደኛውንም “እባክህ ልጄ በጣም ሰነፍ ስለሆነ እኔ ስሞት ያለኝን ንብረት ሁሉ ገብሴን፣ በቆሎዬንና፣ኦቾሎኒዬን ትቼለት መሞት አልፈልግም፡፡ ከሞትኩ ምንም ሳትፈራ ቤቴን፣ ንብረቴንና ፣ጥራጥሬዎቼን አቃጥላቸው፡፡ ከሞትኩ በኋላ እርሻዬን፣ልጆቼንም ሆነ ሚስቶቼን መውሰድ ስለማልችል ልጆቼና ሚስቶቼ ሲቀሩ ሁሉንም ነገር አቃጥልና ለሰነፉ ልጄ ልጆቼንና ሚስቶቼን ስጠውና ሁሉንም መመገብ እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ ይየው፡፡” አለው፡፡ እናም ከሞተ በኋላ ጓደኛው እንደተባለው አደረገ፡፡ አባትየው ከሞተ በኋላ ልጁ ሰነፍ ሆኖ እንዲቀጥልና ንብረት እንዲወርስ አልፈለገም፡፡ ስለዚህ ከአባቱ ሞት በኋላ የአባቱ ጓደኛ ጥራጥሬዎቹንና ቤቶቹን በሙሉ ስላቃጠላቸው ልጁ የራሱን ቤቶች በመስራት ጠንካራ ሠራተኛ በመሆን ብዙ ምርት ስላመረተ የአባቱ አገልጋዮችም በእርሱ ሥር ሆኑ፡፡ እርሱም ጠንክሮ የመስራትን ዋጋ ተምሮ የህዝቡን ከበሬታ አገኘ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|