አጌንጋና ጓደኛው
በክዎት አዋክ የተተረከ
አጌንጋና ጓደኛው ማር ለመሰብሰብ ወደ ጫካ ይሄዳሉ፡፡ እዚያም እንደደረሱ ጓደኛው ምንም ማር መሰብሰብ ስላልቻለ አጌንጋ ጓደኛውን እዛፉ ስር ትቶት ዛፉ ላይ በመውጣት ማሩን ከቀፎዎቹበአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች የማር ቀፎዎችን ዛፍ ላይ መስቀል የተለመደ ነው፡፡ ላይ ራሱ ሰበሰበ፡፡ ማሩንም ሰብስቦ ከጨረሰ በኋላ ይበላው ጀመር፡፡
ጓደኛውም “ለኔስ ለምን ትንሽ ማር አትወረውርልኝም? መወርወር ካልፈለክ ደግሞ ውረድና አብረን እንብላ፡፡” አለው፡፡
አጌንጋም “በመጀመሪያ ማር እንዴት እንደሚሰበሰብ አላውቅም አልክ፡፡ ማር ከፈለግክ ዛፉ ላይ ውጣና እዚህ ብላ፡፡” አለው፡፡
ጓደኛውም እንዲህ አለ “በመጀመሪያ ማር እንደምትወረውርልኝ ነግረኸኝ ነበር፡፡ ካልወረወርክልኝ ልበቀልህ እሞክራለሁ፡፡”
ይህንንም ካለ በኋላ የማገዶ እንጨት ሰብስቦ ከዛፉ ስር እሳት ማቀጣጠል ጀመረ፡፡ ጭሱም እየጨመረ ሲሄድ አጌንጋ ማስነጠስ ጀመረ፡፡
እንዲህም አለ “እባክህ ጭሱን ቀንስልኝና ማር እወረውርልሃለሁ፡፡”
“በመጀመሪያ ወርውርልኝና ከዚያም ጭሱን እቀንስልሃለሁ፡፡” አለው ጓደኛው፡፡
በዚህን ጊዜ አጌንጋ ማር ለጓደኛው ከወረወረ በኋላ ጓደኛው ማሩን እየበላ “በል አሁን የቀረውን ማር ይዘህ ውረድ፡፡ ጓደኛማቾችም ስለሆንን እርስ በርስ በመተማመን መተጋገዝ አለብን፡፡” አለው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|